Wednesday, July 26, 2023

About Dessie Hospital

Dessie hospital is a comprehensive specialized hospital located in Dessie, Ethiopia. Dessie is a town in north-central Ethiopia. Located in the South Wollo Zone of the Amhara Region, it sits at a latitude and longitude of 11°8′N 39°38′E, with an elevation between 2,470 and 2,550 meters above sea level. Dessie is 400 km to the north of the capital Addis Ababa. It has a population of more than 200,000 people.

History

Dessie hospital was established in 1942 in Dessie town around "Kurkur" area. the time was immediately after the defeat of the fascist Italian army by the Ethiopian "Arbegnoch". Currently the historical place is found at the Moha soft drinks factory. The then hospital was constructed from timber. In 1962 the hospital was transferred to it's current location. The hospital landed on 26,940 sq.m land and the construction was jointly funded by the governments of Ethiopia and US. The funding and construction was facilitated by Prince Asfaw Wossen Haile Selassie. For his contribution Emperor Haile Selassie named the hospital in the princes' name as "Asfaw Wossen Haile Selassie Hospital". 

In addition to the health services to the community, the hospital was engaged in training of "Dressers" at the time. In 1977 a physician by the name Dr. Tamrat Reta coordinated a fund from Gutenberg Orphan Relief Fund (GORF), people of Wollo and other financiers to construct "Wollo Children's Hospital". Although the children's hospital was in the compound of the former hospital it was administered independently until 1988. The children hospital had inpatient and outpatient services to children in particular. At the time the children's hospital was the first of its kind outside of Addis Ababa to give children specialty health service. Finally in 1988 it was merged with the parent hospital. Dessie hospital was promoted to referral hospital level in 2005 and to a comprehensive specialized hospital level in 2020.

Current Status

Currently the hospital serve more than 11 million people. Its geographical catchment area includes south Wollo zone, North Wollo zone, Wag Hemra zone, Oromia Special zone, northern parts of North Shewa zone, southern parts of Tigray region, parts South Gondar zone, and parts of Afar region. 

Catchment map of DCSH. the thick red line shows the approximate outline of the catchment area
Source: UN Office for the Coordination of Humanitarian Affairs

The hospital has more than 700 medical professionals and more than 250 administrative personnel working to deliver the best possible care for the community it serves. It houses 597 inpatient beds with more than 15 specialty and sub-specialty services. In collaboration with Wollo University the Hospital is teaching center for medical and other health schools. Additionally the hospital serves as an area of medical practices for students from private and other government colleges. 

Dessie hospital compound from Google Earth
Green arrow head: main compound entrance
Red arrow head: Emergency entrance
  1. Biomedical engineering unit
  2. Radiology unit
  3. Major and minor operating rooms
  4. Oncology unit
  5. Emergency unit
  6. Female medical ward
  7. Orthopedics ward
  8. Pharmacy store
  9. Family medicine and palliative care clinic
  10. Adult outpatient units
  11. Comprehensive diagnostic unit (under construction)
  12. Maternal and child health center
  13. Administrative units
  14. Medical and surgical wards
  15. Store and library
  16. Parking area



Thursday, July 20, 2023

የአዙሪት በሽታ እንቅስቃሴ (BPPV)


ይህ የአካል እንቅስቃሴ የብራንት ዳሮፍ እንቅስቃሴ ይባላል። ድንገት እየመጣ በዙሪያቸው ያለውን ነገር እያሽከረከረ ለሚያስቸግር የአዙሪት በሽታ የሚታዘዝ እንቅስቃሴ ነው። ይህ የአዙሪት በሽታ (Benign Paroxysmal Positional Vertigo (BPPV)) በውስጠኛው የጀሮ ክፍል በሚፈጠር ጠጠር ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው። እንቅስቃሴውም ጠጠሩን በማስረግ እየተንከባለለ አዙሪቱን እንዳያስከትል ያደርጋል። ሌሎች ውስብስብ እንቅስቃሴዎች በዶክተሩ የሚሰሩ ቢኖሩም፣ ይህኛውን የእንቅስቃሴ አይነት ተመራጭ የሚያደርገው በቀላሉ በቤት ውስጥ መሰራት መቻሉ ነው። 

ህመምተኛው በ1 ቁጥር እንደሚታየው ቍጭ ትልና ወደጐን ትተኛለች፣ አዙሪት ከተነሳ እስኪበርድ መጠበቅ ከዛ ቀጥ ብሎ መቀመጥና በተቃራነው ጐን ይህንን መድገም። በማንኛውም ሰአት አዙሪቱ (Vertigo) ከተነሳ ባለበት መሆንና እስኪበርድ መጠበቅ አለበት። ይህንን እንቅስቃሴ በአንድ ጊዜ ከ10 እስከ 20 ጊዜ፤ በቀን እስከ 3 ጊዜ መደጋገም አለበት። አዙሪት በሽታው እስከሚለቅ ድረስ በዚህ መልኩ እንቅስቃሴው መሰራት አለበት።

የትከሻና ጉልበት ህመም እንቅስቃሴ



በተለያዩ ጥናቶች እንዳታየውና በልምድም እንደ ተመለከትነው፣ የሰነበቱና የዘወተሩ የትከሻና የጉልበት ህመሞችን ለመቆጣጠር ማገገሚያ እንቅስቃሴዎች ከመድሀኒቶችና ኦፕሬሽኖች የተሻለ አቅም አላቸው። የሚከተሉት ምስሎች ለትከሻ ና ጉልበት ህመሞች በቀላሉ በቤት ውስጥ መሰራት የሚችሉ ናቸው። የዚህ አይነት ችግር ለገጠማቸው ጓደኞችዎና ቤተሰቦችዎ ያጋሯቸው።

Plantar Fasciitis (የተረከዝ ውጋት)



የተረከዝ ውጋት (Plantar Fasciitis) የውስጠኛው እግር መወጠሪያ ቋንጃ በመቆጣቱ ምክንያት የሚመጣ ህመም ሲሆን፣ ለምንና እንዴት እንደሚመጣ በውል አይታወቅም። ህመሙ ጧት የመጀመሪያ እርምጃዎች ላይ እንደ ጦር ጠቅ እያደረገ የመውጋት ስሜት አለው። ይህ ህመም በእንቅስቃሴና ውጥረት ህክምናዎች ፣ እንደሁም ከስላሳ ሲሊከን የተሰራ የተረከዝ ፓድ በመጠቀም በተወሰኑ ሳምንታት ውስጥ ይጠፋል።

What is Family Medicine and Family Doctor?


Family medicine is a medical specialty within primary care that provides continuing and comprehensive health care for the individual and family across all ages, genders, diseases, and parts of the body.

The names of the specialty emphasize its holistic nature and/or its roots in the family. It is based on knowledge of the patient in the context of the family and the community, focusing on disease prevention and health promotion. According to the World Organization of Family Doctors (WONCA), the aim of family medicine is "promoting personal, comprehensive and continuing care for the individual in the context of the family and the community".

The specialty focuses on treating the whole person, acknowledging the effects of all outside influences, through all stages of life. Family physicians will see anyone with any problem, but are experts in common problems. 

Family physicians complete an undergraduate degree, medical school, and three more years of specialized medical residency training in family medicine. Their residency training includes rotations in internal medicine, pediatrics, obstetrics-gynecology, psychiatry, surgery, emergency medicine, and geriatrics, in addition to electives in a wide range of other disciplines.

ሀኪም


ከሀኪም በበለጠ ኃላፊነትና ሙያዊ ግዴታ በብዙ ሰዎች ትከሻ ላይ አይወድቅም። በህመምና ስቃይ ላይ ያለን ሰው ማከም ቴክኒካል ብቃትን፣ ሳይሳዊ ዕውቀትንና የሰዉን ማንነት መረዳትን ይጠይቃል። ጥበበኝነትና ርህራሄ ከሀኪም የሚጠበቁ ነገሮች ናቸው። ይህም የታመመ ሰው የተበላሹ የሰውነት ስራዎችና የበሽታዎች ጥርቅም ብቻ ሳይሆን፤ ስጋትና ተስፋ፣ ፍርሀትና መደናገጥ ያሉት ሙሉ ሰዉ ነዉ። በመሆኑም ከመድሀኒትና ሰርጀሪ ተጨማሪ መንፈሳዊ ድጋፍና እንክብካቤ ይፈልጋል።

Harrison’s Principles of Internal Medicine, 1950


ምስል: "The Doctor" የተሰኘው የሉክ ፊልድስ ስዕል ነው። ፊልድስ ታዋቂ እንግሊዛዊ ሰአሊ ሲሆን፣ ይህን ስዕል በ1891 ዓ.ም አጠናቀቀ።

Wednesday, July 12, 2023

ራስ ምታት


ራስ ምታት የሚባለው ህመም በፊት በራስ ቅልና አንገት አካባቢ የሚከሰት የህመም ስሜት ሲሆን በጣም የተለመዱና በህብረተሰቡ ውስጥ በብዛት ከሚከሰቱ የህመም አይነቶች አንዱ ነው። በአማካይ በአንድ አመት ውስጥ ግማሽ ያክሉ በአዋቂ እድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎችን ያጠቃል። በአጠቃላይ ወደ 200 ሚያክል የራስ ምታት አይነቶች ያሉ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት ለህይወት አስጊ ናቸው። አብዛኞቹ ግን ከሚያደርሱት ህመምና ስቃይ ውጪ ለህይወት አስጊ አይደሉም። ከእነዚህ ራስ ምታት አይነቶቹ ዓይነቶች ውስጥ በጣም የተለመዱትና በተደጋገሚ የሚከሰቱት ሁለት አይነት ራስ ምታቶች ናቸው። እነሱም ወጣሪ ራስ ምታት (Tension headache) ና ሚግሬን ራስ ምታት (Migraine headache) ናቸው። 

  • ወጣሪ ራስ ምታት (Tension headache) – ይህ የራስ ምታት አይነት ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው በእራስ ቅል ዙሪያ ጠብቆ የታሰረ ጥምጣም የሚያስከትለውን አይነት ውጥረትና ህመም የሚያመጣ የራስ ምታት ነው። 

  • ሚግሬን ራስ ምታት (Migraine headache) – ይሀኛው አይነት ራስ ምታት የራስ ቅልን አንድ ጐን ለይቶ የሚያም ሲሆን የህመሙ አይነትም ተደጋጋሚ የሆነ የመደብደብና በጦር ወይም በእንጨት የመወጋት አይነት ስሜት ነው። ህመሙ ከባድ ከመሆኑ የተነሳ ሰዎች የቀን ተቀን ስራቸውን ለመተግበር ይቸገራሉ። መራመድ ወይም ደረጃ መውጣት ህመሙን ያባብሰዋል። ማቅለሽለሽና ማስታወክ እንዲሁም ድምፅ ወይም ብርሃን መፍራት ሊኖረው ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ሊጀምር ሲል በአይናቸው የተለያዩ ቀለማት ወይም ቀስተ ደመና ሊታያቸው ይችላል። 

እራስ ምታት ሲነሳብኝ፣ እንዲሻለኝ ማድረግ የምችለው ነገር አለ ወይ? 

  • አዎ የሚከተሉትን ነገሮች መሞከር ይችላሉ። ብዙ ሰዎችም በነዚህ እርምጃዎች ራስ ምታታቸው ይታገስላቸዋል።

  • ያለ ሀኪም ትዛዛዝ የሚገኙ የህመም ማስታገሻዎች፣ አንደ ፓራስታሞል፣ አይቡፕሮፌን፣ ዲክሎፌናክና ኢንደሜታሲን የመሳሰሉት መድሀኒቶች ከፋርማሲ ገዝቶ መውሰድ።

  • በቀዝቃዛ፣ ጨለም ያለና ፀጥታ የሰፈነበት ከፍል ውስጥ አረፍ ማለት። ይሄ በተለይ ለሚግሬን ራስ ምታት በጣም አስፈላጊ ነው።

የራስ ምታት ህክምና ምንድን ነው?

  • የራስ ምታት ህክምና 2 አላማ አለው፣ የመጀመሪያው አደገኛ አይነት ራስ ምታት እንዳልሆነ ማረጋገጥ። እነዚህ ራስ ምታቶች የጭንቅላት ደም መፍሰስ፣ ማጅራት ገትርና የመሳሰሉት ለህይወት አስጊ ራስ ምታቶችን መለየት መሰረታዊ የህክምናው አላማ ነው። ሁለተኛው አላማ ራስ ምታቱን መቆጣጠር ነው። ይህንን ለማድረግ ከላይ የተጠቀሱትን የማስታገሻ መድሀኒቶችና በሃኪም ብቻ የሚታዘዙ ሌሎች መድሀኒቶችን መጠቀም ያስፈልጋል።


ዶ/ር ካሊድ መሀመድ MD MBA
Family Medicine

About Dessie Hospital

Dessie hospital is a comprehensive specialized hospital located in Dessie, Ethiopia. Dessie is a town in north-central Ethiopia. Located in ...