ይህ የአካል እንቅስቃሴ የብራንት ዳሮፍ እንቅስቃሴ ይባላል። ድንገት እየመጣ በዙሪያቸው ያለውን ነገር እያሽከረከረ ለሚያስቸግር የአዙሪት በሽታ የሚታዘዝ እንቅስቃሴ ነው። ይህ የአዙሪት በሽታ (Benign Paroxysmal Positional Vertigo (BPPV)) በውስጠኛው የጀሮ ክፍል በሚፈጠር ጠጠር ምክንያት የሚመጣ በሽታ ነው። እንቅስቃሴውም ጠጠሩን በማስረግ እየተንከባለለ አዙሪቱን እንዳያስከትል ያደርጋል። ሌሎች ውስብስብ እንቅስቃሴዎች በዶክተሩ የሚሰሩ ቢኖሩም፣ ይህኛውን የእንቅስቃሴ አይነት ተመራጭ የሚያደርገው በቀላሉ በቤት ውስጥ መሰራት መቻሉ ነው።
ህመምተኛው በ1 ቁጥር እንደሚታየው ቍጭ ትልና ወደጐን ትተኛለች፣ አዙሪት ከተነሳ እስኪበርድ መጠበቅ ከዛ ቀጥ ብሎ መቀመጥና በተቃራነው ጐን ይህንን መድገም። በማንኛውም ሰአት አዙሪቱ (Vertigo) ከተነሳ ባለበት መሆንና እስኪበርድ መጠበቅ አለበት። ይህንን እንቅስቃሴ በአንድ ጊዜ ከ10 እስከ 20 ጊዜ፤ በቀን እስከ 3 ጊዜ መደጋገም አለበት። አዙሪት በሽታው እስከሚለቅ ድረስ በዚህ መልኩ እንቅስቃሴው መሰራት አለበት።
No comments:
Post a Comment