ከሀኪም በበለጠ ኃላፊነትና ሙያዊ ግዴታ በብዙ ሰዎች ትከሻ ላይ አይወድቅም። በህመምና ስቃይ ላይ ያለን ሰው ማከም ቴክኒካል ብቃትን፣ ሳይሳዊ ዕውቀትንና የሰዉን ማንነት መረዳትን ይጠይቃል። ጥበበኝነትና ርህራሄ ከሀኪም የሚጠበቁ ነገሮች ናቸው። ይህም የታመመ ሰው የተበላሹ የሰውነት ስራዎችና የበሽታዎች ጥርቅም ብቻ ሳይሆን፤ ስጋትና ተስፋ፣ ፍርሀትና መደናገጥ ያሉት ሙሉ ሰዉ ነዉ። በመሆኑም ከመድሀኒትና ሰርጀሪ ተጨማሪ መንፈሳዊ ድጋፍና እንክብካቤ ይፈልጋል።
Harrison’s Principles of Internal Medicine, 1950
ምስል: "The Doctor" የተሰኘው የሉክ ፊልድስ ስዕል ነው። ፊልድስ ታዋቂ እንግሊዛዊ ሰአሊ ሲሆን፣ ይህን ስዕል በ1891 ዓ.ም አጠናቀቀ።
No comments:
Post a Comment